Skip to main content
zena10

ሐምሌ 5/2016 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸም እየገመገመ ነው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ባይዳ ሙንዲኖ እና ሌሎች የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸም ለቋሚ ኮሚቴው ዝርዝር ሪፖርት እየቀረበ ነው። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው ዋሌራ እና ሌሎች የቋሚ ኮሚቴው አባላት በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት ያደርጋሉ።