ቀን 25/10/2016 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሴቶች ህፃናት ጉዳይ ቢሮና የሴት አደረጃጀቶች የጋራ ፎረም የ2017 እቅድ ላይ ውይይት አደረጉ። የሴቶች ሊግ፤ማህበር እና ፌድሬሽን ሰብሳቢዎች ተገኝተው ለሴቶች ተሳታፊነ፣ተጠቃሚነት ላይ በ2017 በትኩረት መሰራት በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል ። የፎረሙ ሰብሳቢ እና የሴቶችና ህጻናት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ በይዳ ሙንዲኖ እንዳሉት ባለፈው በጀት አመት የሴት አደረጃጀትን በመጠቀም በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል እነዚህም የሴቶች ልማት ህብረት በአዲስ መልኩ መቋቋሙ በዚህም 1,123,592 ሴቶችን ማደራጀት መቻሉ 347 ሺህ በላይ ሴቶች የቁጠባና የብድር አገልግሎት በማግኘት ወደ ገቢ ማስገኛ መሰማራታቸው እና የጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን መከላከል ላይ በርካታ ስራዎች የተሰሩ መሆኑ የማርች 8 ንቅናቄ ላይ አቅመ ደካማ ለሆኑ ሴቶችና ህጻናት ድጋፎችን ማድረግ እና ሴቶች ሰላም ማስፈን ላይ ከ700 መቶ ሺህ በላይ ውይይት ያደረጉበት እና የት/ት ስብረትን ለመቀነስ ለተማሪዎች የመጽሀፍ ግዢ የሚሆን ሀብት የማሰባሰብ ስራዎች ከብዙ በጥቂቱ የተከናወኑ ተግባራት ናቸው ። የሴቶች አደረጃጀቶች ዋነኛ አላማ ሴቶች መብትና ደህንነታቸውን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ሴቶች በመደራጀት የኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና የፖለቲካው መስኮች ለይ ተሳታፊም ተጠቃሚም መሆን ስለሚገባቸው መላ የክልላችን ሴቶች በተዘረጉ የሴቶች አደረጃጀቶች ማለትም የሴቶች ልማት ህብረት አደረጃጀት የሴቶች ማህበር እና የሊግ አደረጃጀት ላይ እንዲደራጁ (እንዲታቀፉ) ማድረግ እንደሚገባ አንስተዋል። በጋራ ፎረሙ የነበሩ የአደረጃጀት ሀላፊዎችም ቀጣይ መላ ሴቶችን ተጠቃሚ በሚያደርግ መንገድ አደረጃጀቶችን የማጠናከር የንቅናቄ ስራዎችን በቅንጀት መስራት የክረምት በጎ ስራዎችን የተቀናጀ የድጋፍ ክትትል ስራዎችን እና አፈጻጸምን በጋራ እየገመገሙ መሄድ እንደሚገባ ሰፊ ውይይት በማድረግ አጠቃለዋል ። ዘገባው የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ነው!!